የአፍ ውስጥ የመንጋጋ እና የፊት ቀዶ ህክምና
Oral and Maxillofacial surgery(OMFS)
የህክምና ዘርፍ:የሚያክማቸው ችግሮች:ስልጠና እና አገልግሎት በኢትዮጵያ
ዶ/ር ፉአድ መሀመድ | DMD,OMFS
የአፍ:የመንጋጋ እና ፊት ቀዶ ህክምና
ስፔሻሊስት
OMFS ምንድነው?
*በእግሊዝኛ መጠሪያው ‘Oral and Maxillofacial surgery'(OMFS) ተብሎ ሲታወቅ;
*በዋነኝነት በአፍ ውስጥ በመንጋጋ አጥንቶች እና ፊት ላይ የሚያጋጥሙ የጤና ችግሮችን (ህመሞችን) የሚመረምር;የሚለይ እና
እንዲሁም በዋነኝነት በቀዶ ህክምና የሚያክም/የሚያስተካክል የህክምና ዘርፍ ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ የመድሃኒት እና ሌሎችንም
የህክምና መንገዶች ይጠቀማል
የሚያክማቸው ዋና ዋና ችግሮች
*የአፍ ውስጥ: የመንጋጋ እና የፊት ላይ ዕጢዎች- ከቀላል እስከ ከባድ (ካንስር ደረጃ የደረሱ) ህመሞችን
*የመንጋጋ እና የፊት አጥንት ስብራት እና ጉዳቶችን
*የመንጋጋ መገጣጠሚያ ችግሮችን(TMD)
*የአፍ እና ፊት ላይ ነርቭ ችግሮች/ህመሞች
*የምራቅ አመንጪ አካለት(Salivary glands)በሽታዎች እና እጢዎችን
*የተፈጥሮ /ከአፈጣጠር ጋር ተያይዘው አፍ እና ፊት ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን;
-የከንፈር እና ላንቃ መሰንጠቅ(Cleft lip and palate )
-የአጥንት እድገት አለመመጣጠኖች.( Facial /jaw deformities )
*ሌሎች የሚያክሟቸው ሁኔታዎች
ሌሎች የሚያክሟቸው ሁኔታዎች
-የአፈንጫ ሳይንስ(paranasal sinus)ችግሮች -አፍ ውስጥ እና ፊት ላይ የሚከሰቱ ጉዳቶችን
-የአፍ ውስጥ የፊት እና አንገት ላይ ኢንፌክሽኖችን:
-አገጭ ስር እና አንገት ላይ የሚወጡ እብጠቶችን(ዕጢዎችን) :
-የተለያዩ የአፋ እና ፊት ቀዶ ህክምና ምርመራዎች እና ማስተካከያዎች
የስፔሻሊቲ ስልጠናው
*የOMFS ስልጠና እንደየሀገሩ የትምህርት ካሊኩረም ይለያያል።
*በአንዳንድ ሀገራት(ለምሳሌ;በአውሮፓ አካባቢዎች) የመጀመሪያ ድግሪ በጠቅላላ ህክምና እና በጥርስ ህክምና (ሁለቱንም ድግሪ ግዴታ) ካገኙ
ቡሀላ የሚሰጥ ሲሆን
በሌሎች ሀገራት (ለምሳሌ ህንድ:አሜሪካ:እንዲሁም በሀገራችን ኢትዮጵያ) ደግሞ ከጥርስ ህክምና የመጀመሪያ ድግሪ በኋላ የስፔሻሊቲ
ስልጠናው ይሰጣል ።
* የስፔሻሊቲ ሰልጠናው እንደየሀገሩ ከ4 -6 ዓመት ሊፈጅ ይችላል
OMFS – በዓለም አቀፍ ደረጃ
*በዓለም አቀፍደረጃ ከ1860ዎቹ(USA) ጀምሮ ራሱን የቻለ የህክምና ዘርፍ መሆን ጀመረ።
*ከዚያ በኋላ የአፍ ውስጥ የመንጋጋ እና የፊት ቀዶ ህክምና በተለያዩ የህክምና ስርዓቶች ውስጥ እየተስፋፋ መጥቷል።
OMFS – በኢትዮጵያ
*በሀገራችን ኢትዮጵያ የ’OMFS’ ስፔሻሊቲ ስልጠና መሰጠት ከተጀመረ ከ 15 ዓመታት በላይ ዘልቋል::
*በአሁኑ ሰአት በዋነኝነት የሰፔሻሊቲ ስልጠናው የሚሰጥባቸው ተቋማት
:ቅ/ጳ/ሆ/ሚ/ሜ ኮሌጅ
:ጅማ ዩንቨርሲቲ
:መቀሌ ዩንቨርሲቲ
:አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ
:የካቲት ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ እና
:ሀዋሳ ዩንቨርስቲ
የ OMFS ስፔሻሊስቶች በኢትዮጵያ
*በዚ ሰአት በሀገራችን በአጠቃላይ ወደ 100 ገደማ የሚጠጉ የዚህ ህክምና ዘርፍ ስፔሻሊስት ሀኪሞች በተለያዩ የህክምና
ተቋማት እያገለገሉ ይገኛሉ።
ዶ/ር ፉአድ መሀመድ DMD,OMFS
የአፍ:የመንጋጋ እና ፊት ቀዶ ህክምና
ስፔሻሊስት
